Ethiopia

ተቋማቱ በቁጥጥር የተለዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ አበባ ሪጂን በቁጥጥር ለተለዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።ተቋሙ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስአበባ ሪጂን ላይ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

በአዳማ በነበረው የውይይት መድረክ ተቋሙ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ላይባደረገው የቁጥጥር ስራ ግኝቶችን ያቀረቡት በተቋሙ የአስተዳደር በደል መቆጣጠር ዳሬክተር አቶ አዳነ በላይ ናቸው።ሰፊ የደንበኞች ቅሬታ ከሚነሳባቸው ተቋማት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አንዱ መሆኑን ያወሱት አቶ አዳነ ባለስልጣኑ ሰፊ ክፍተቶች ቢኖሩበትም በበጎ የሚነሱ ተግባራት እንዳሉትም ተናግረዋል።ባለስልጣኑ በውሃ ተደራሽነት፣ በፈረቃ ካርታ ዝግጅት፣ ከደንበኛ ፎረም ጋር አብሮ መስራት እንዲሁም ውስጥና የውጭ ቅሬታ አፈታት በመልካም ጎን የሚነሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የውሃ እጥረትና ብክነት፣ የቅንጅታዊ አሰራር ጉድለት፣ የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ እጥረትና በሰራተኞች ዲሲፕሊን በኩል ለሚነሱ ክፍተቶች ደግሞ ባለስልጣኑ ፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጣቸው የሚገቡ ናቸው ብለዋል። በተለይም በሌለ የውሃ ሽፋን የሚቀርቡ ሪፖርቶች እርምት ሊወሰድባቸው ይገባል ሲሉ አመልክተዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button