Ethiopia

የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ዉጪ በተቀሩ ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ19 የቀዉስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ ፡፡

ከጥቅምት 30 ጀምሮ ይጀመራል የተባለዉ ትምህርት አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስኪጠናቀቁ ድረስ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ነዉ ቢሮው ያስታወቀዉ፡፡ከባለፈው ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በመሰጠት የጀመረው የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የገጽ ለገጽ የክለሳ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button