Africa

ሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላን በሶሪያ ሰማይ ተሰውሯል

አርትስ 08/01/2011
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው አይ ኤል 20 የተሰኘ የጦር ጀት በሜዲትራኒያን ባህር አካባቢ ከራዳር ውጭ በመሆን ነው ደብዛው የጠፋው፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው 14 ሰዎችን ያሳፈረው አውሮፕላን በተሰወረበት አካባቢ የእስራኤል እና የፈረንሳይ አየር ሀይሎች ድብደባ ሲያካሂዱ ነበር፡፡
የሩሲያ መንግስት እስካሁን አውሮፕላኑ በምን ምክንያት ሊሰወር እንደቻለ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል ነው የተባለው፡፡
የእስራኤሉ ሃረትዝ ደግሞ አሜሪካ አውሮፕላኑን የሶሪያ መንግስት ወታደሮች በፀረ አውሮፕላን መሳሪያ ተኩሰው ጥለውታል ማለቷን ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button