EconomyEthiopia

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን የገለጸዉ  የቆዳው ዘርፍ የሚመራበት ፍኖተ ካርታን አስመልክቶ በተካሄደ ዉይይት ላይ ነዉ፡፡

ፍኖተ-ካርታው በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣በኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር እና በኢንተርፕራይዝ ፓርትነር የተዘጋጀ ነዉ፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየስ በዉይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቷ  ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለምታደርገው መዋቅራዊ ሽግግር ትልቅ እርምጃ ነዉ ብለዋል፡፡

የቆዳው ዘርፍ የሚመራበት ፍኖተ ካርታን አስመልክቶ በተካሄደ ዉይይትም አገራችን ከፍተኛ የእንሰሳት ሃብት እንዳላት የገልፁት አቶ ተካ  ይህም የቆዳን ኢንዱስትሪ  ወደፊት ለማስወንጨፍ መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የቆዳን ኢንዱስትሪ ልማትን ለማሳካት የግብርና ልማት እና የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን እርስ በእርስ ሊመጋገቡ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ፤ሁለቱ ሴክተሮች ተመጋግበውና ተናበው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል፡፡

ሌላው በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀ የዚህ ፍኖተ-ካርታ መዘጋጀት ንዑስ ዘርፉን ለማሳደግ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ከ12 ያላነሱ  ቆዳ ፋብሪካዎች በአቅም ዕጦትና በዕዳ መዘጋታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ መንግሥት ተግባራዊ ሲያደርገው የቆየው ፖሊሲ ከስድስት ዓመታት በላይ የሆነውና እሴት የተጨመረበት ብሎም ያለቀለት ቆዳ ወደ ውጭ እንዲላክ የሚያስገድድ ነው፡፡

ይህ ፖሊሲ በከፊል ያለቀለትና ከጥሬ ቆዳ ደረጃ ጥቂት ማሻሻያ የተደረገበት ምርት ወደ ውጭ እንዳይላክ ለማገድ፣ የ150 በመቶ የወጪ ንግድ ታክስ ማወጁ ኢንዱስትሪውን በተለይም የአገር ውስጥ ፋብሪካዎችን ለአደጋ እንዳጋለጠ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button