Breaking News

ሞሮኮና አልጀሪያ ህገ ወጥ ስደትን ለማስቆም የፋይናንስ እጥረት ፈተና ሆኖባቸዋል 

በቡራዩና አካባቢዋ ተከስቶ በነበረው ችግር ከተጠረጠሩ ሰዎች አምስት ክላሽ እና 12 ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ዋለ አርትስ 10/01/2011 በቡራዩ እና አካባቢዋ ተከስቶ በነበረው ችግር የተጠረጠሩ 46 ሰዎች ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ፥ ከተጠርጣሪዎቹ እስከአሁን አምስት ክላሽ እና 12 ሽጉጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ገልፀዋል፡፡ በግጭቱ ተጎድተው ከነበሩ ሰዎች መካከል የሦስት ሰዎቸ ህይወት ማለፉን ገልጸው በአጠቃላይ እስከአሁን የሟቾቹ ቁጥር 26 መድረሱን ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡ በግጭቱ ወቅት ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የጸጥታ አካላትና የስራ ኃላፊዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡ ከተፈናቃዮቹ መካከል 50 ግለሰቦች ወደ ቡራዩ በመሄድ ከከተማ መስተዳድር አመራሮችና እና ከሽማግሌዎች ጋር ወደ ቀያቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል፡፡

አርትስ 10/01/2011
ሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገሮች እየተባባሰ የመጣውን ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል በጋራ እንሰራለን ቢሉም የኢኮኖሚ አቅማቸው እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡
የፈረንሳዩ ሳምንታዊ መጽሄት ኤል ኤክስፕረስ እንደዘገበው የፓሪስ መንግስት ሞሮኮና አልጀሪያን ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርቧል፡፡
የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዠራርድ ኮሎምቦ ከመጽሄቱ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልለስ ሁለቱን ሀገሮች እንደ መሸጋገሪያ ተጠቅመው ወደ አውሮፓ የሚገቡትን ስደተኞች ለማስቆም በፋይናንስ ልንደግፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ባለፉት 8 ወራት ብቻ ከሞሮኮ ተነስተው በስፔን በኩል አቋርጠው ወደ አውሮፓ የገቡት ህገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር 33 ሺህ 795 መሆኑ የችግሩን ስፋት ያሳያል ብለዋል ኮሎምቦ፡፡

leave a reply