Ethiopia

አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል። አቃቤ ህግም በችሎቱ ተገኝቶ እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚል እና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመረ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል። አቶ ልደቱ አያሌው በበኩላቸው “የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ በመንግስት ደረጃ አስገብቼው ተቀባይነት የለውም ተብዬ ያስቀመጥኩት ነው፤ ተጠያቂነት ቢኖረው ኖሮ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብሎ ዝም አይለኝም ነበረ” ብለዋል።

ሁለተኛው ማለትም “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚለውም ቢሆን በረቂቅ ላይ ያለ ያልታተመ ነው፤ ልከሰስ የምችለው ሰነዱን አሳትሜ አሰራጭቼ ቢሆን ነበረ፤ በዚህች ሀገር ላይ ሳንሱር የለም ስለዚህ ሀሳቤን ነው እየገለፅኩ ያለሁት፤ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሊረዳልኝ ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል። “ውጭ ሀገር ሄጄ የታከምኩት ሀብታም ነጋዴ ሆኜ ሳይሆን፤ ህክምናው እዚህ ስለሌለ ነው፤ ይህንን ፍርድ ቤቱ ከግምት ያስገባልኝ” ሲሉም ጠይቀዋል። የአቶ ልደቱ አያለው ጠበቃም ለደንበኛቸው ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል። የቢሾፍቱ ከተማ አቃቤ ህግ በበኩሉ፥ አቶ ልደቱ አያሌው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ አመጽና ሁከት በመቀስቀስ በህገ ወጥ መንገድ የመንግስት ምስረታ ለማከናወን
አቅደው በመንቅሳቀስ ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸውን ለችሎቱ ገልጿል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሁለቱን ክርክር የተከታተለው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button