EthiopiaPoliticsRegionsSocial

የኦዴፓ ዘጠነኛ ጉባዔ ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳን ም/ሊቀመንበር አድርጎ ተጠናቀቀ

አርትስ 11/01/2011
ለሦስት ቀናት በጅማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ጉባዔ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ በዚህ ድርጅቱ ስያሜ፣ አርማና መዝሙሩን በቀየረበትና ትናንት ደግሞ ነባር አባላቱን በክብር ባሰናበተበት ጉባዔው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ይፋ አድርጓል ፡፡ ከዚህ ባሻገር በጉባዔው ማጠቃለያ ለድርጅቱ ስራ አስፈፃሚነት ዶ/ር አብይ አህመድ፣ አቶ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣አቶ አዲሱ አረጋ፣አቶ ፍቃዱ ተሰማ፣አቶ ብርሐኑ ፀጋዬ፣ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ዶ/ር አለሙ ስሜን እና አቶ ሽመልስ አብዲሳን መርጦ ዶ/ር አብይ አህመድ በሊቀመንበርነት እንዲሁም አቶ ለማ መገርሳ በም/ሊቀመንበርነት እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button