AfricaUncategorized

የግብፅ ፍርድ ቤት የ80 ዓመቱን አዛውንት የሞት ቅጣት እንዲፀና ወሰነ

አርትስ 05/03/2011

አዛውንት ሸይክ አብደል ሀሊም ጋብሬልን የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ፍርድ በሞት እንዲቀጡ የወሰነባቸው 13 የግብፅ ፖሊሶች ሲገደሉ እጃቸው አለበት በማለት ነው፡፡

በፈረንጆቹ 2013 ከጋብሬል ጋር በተቀነባበረ ሴራ ጊዛን ከተማ ውስጥ በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት በማድረስ ወንጀል የተከሰሱ 20 ግለሰቦችም ቀደም ሲል ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አምንስቲ ኢንተርናሽናል አዛውንቱ ጋብሬልን ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ምህረት እንዲያደርጉላቸው ጠይቋል፡፡

ይሁንና አዲሱ የገብፅ ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ይግባኝ መጠየቅን ይከለክላል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ምክንያት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለፕሬዝዳንት አብደልፈታ አልሲሲ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ እንዲፅፍ ጠይቋል፡፡

የገብፅ ወታደራዊና ሲቪል ፍርድ ቤቶች እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠረ ከ2013 ወዲህ 1 ሺህ 400 ሰዎች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button