Breaking News

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከግንቦት 7 ጋር በይፋ መለያየቱን አስታወቀ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በበኩሉ ከየትኛውም ጥምረት አልተለየሁም አለ

አርትስ 14/01/2011
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በትናንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል። ነገር ግን ንቅናቄው የተሰጠው መግለጫ ህጋዊነት የጎደለው ነው ብሏል፡፡
የግንባሩ ሰብሳቢ አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ እንደተናገሩት፥ ከግንቦት ሰባት ጋር በአመራር አሰጣጥ እንዲሁም በፋይናስ አሰራር ላይ ባለ ክፍተት ምክንያት ለመለያየት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
የአርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምሳሉ ፀጋ ናቸው ንቅናቄው ከየትኛውም ጥምረት አልተለየም ያሉት፡፡

leave a reply