EthiopiaTech

የኢኖቬሽን ማዕከሉ ግንባታ ከ50 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

የኢኖቬሽን ማዕከሉ ግንባታ ከ50 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቡራዩ ከተማ ላይ እያስገነባው ያለው የኢኖቬሽን ማዕከል ግንባታ ከ50 ከመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡
ማዕከሉ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች እንዲማሩበት ታስቦ የተገነባ ነዉ፡፡
አሁን ግን ልዩ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ማዕከሉ ገብተው የፈጠራ ስራዎቻቸውን አዳብረው ወደ ምርት ቀይረው እንዲወጡ የሚያስችል ተደርጎ ያደገ ነው፡፡
የግንባታ ሂደቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትለሰው ሃብት ቴክኖሎጂና መገናኛ ቋሚ ኮሚቴዎች ተጎብኝቷል፡፡
ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ ከተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ዘግይቷል፡፡
ለመዘግየቱ ደግሞ በአካባቢው ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
ቋሚ ኮሚቴዎቹ ትውልድ ተሻጋሪ የሆነው ይህ ማዕከል ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button