Africa

በኒጀር ፅንፈኛ ሃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 በኒጀር ፅንፈኛ ሃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ:: በሀገሪቱ መንግስት አክራሪ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ቡድኖቹ ጥቃቱን ያደረሱት በማሊ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ በሁለት መንደሮች ነው ተብሏል፡፡ የኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው መንደሮች በማቅናት የጎበኙ ሲሆን የተጎጂ ቤተሰቦችና ነዋሪዎቹን አበረታተዋል፡፡

ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ተዋጊ ሃይሎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ሁለት ተዋጊ ሚሊሻዎቻቸው ከተገደሉባቸው በኋላ ነው፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው በሀገሪቱ ሁለተኛው ዙር ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ ካደረጉ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ኒጄር መሰረቱ ናይጄሪያ የሆነው ቦኩሃራምን ጨምሮ የበርካታ አክራሪ ሀይሎች ጥቃት ሰለባ ከሆነች ውላ አድራለች፡፡

በዚህም ምክንያት በነዚህ ጂሃዲስቶች ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ መቶ ሺዎች ደግሞ ቀያቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ በጂሃዲስቶች በአለመረጋጋት እየተፈተነች ያለችው ኒጄር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ1960 ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ወዲህ የመጀመሪያውን ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button