Africa

በካሜሩን አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ከ80 በላይ ሰዎች ታግተው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል ተባለ

በካሜሩን አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ከ80 በላይ ሰዎች ታግተው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል ተባለ

አርትስ 27/02/2011

 

የካሜሩን ጦር ሃይል እንዳስታወቀው በትናንትናው ዕለት በተፈጸመው በዚሁ እገታ ከ80 የሚበልጡ ሰዎች ባልታወቁ ግለሰቦች ታፍነው ተወስደዋል ።

ከታጋቾቹ አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸው የተነገረ ሲሆን የታፈኑትም ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች በሚበዙበት ሰሜናዊ ምዕራብ ካሜሩን ፣ ባሜንዳ የተባለ ከተማ ውስጥ ከሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው።

ተገንጥለው የራሳቸውን መንግስት መመስረት ከሚፈልጉትና እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ከሚበዙበት የካሜሩን ክልል ይህንን እገታ በተመለከተ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ብሏል ጦር ሃይሉ።

የጦር ሃይሉ ባለስልጣናት ለዜና ወኪሉ እንደገለጹት የታገቱት ዳይሬክተሩን ጨምሮ 81 የትምህርት ቤቱ ሰራተኞችና ተማሪዎች ሲሆኑ ሁሉም ታፍነው ወደጫካ መወሰዳቸውን አውቀናል ብለዋል።

የካሜሩን መንግስት ቃል አቀባይ ሁኔታውን እየተከታተልን ነው ከማለት ውጪ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button