AfricaEthiopiaSport

በአራኛው ዙር የካራባኦ (የሊግ ካፕ) ውድድር ዕጣ ድልድል ይፋ ሆነ

አርትስ ስፖርት 20/01/2011

የአራተኛው ዙር የእንግሊዝ እግ ኳስ ሊግ (ካራባኦ) ውድድር ጨዋታዎች ትናንት ይፋ ሲደረግ ደርቢ ካውንቲን እያሰለጠነ የሚገኘው ፍራንክ ላምፓርድ፤ የቀድሞ ክለቡን ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ የሚገጥም ይሆናል፡፡ ደርቢ በሶስተኛው ዙር በመለያ ምት ማንችስተር ዩናይትድን ጥሎ ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ሁለቱ የለንደን ቡድኖች ዌስት ሀም እና ቶተንሀም በለንደን ኦሎምፒክ ስታዲየም እንደሚገናኙ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሀድ ፉልሀምን ያስተናግዳል፡፡

አርሰናል በሜዳው ፍላይ ኢምሬትስ ብላክፑልን ሲያስተናግድ፤ ሌስተር ሲቲ በኪንግ ፓወር የኢቨርተን እና ሳውዛምፕተንን አሸናፊ የሚገጥም ይሆናል፡፡

በሌሎች ድልድሎች፤ ሚድልስ ብራ ከ ክሪስታል ፓላስ፣ በርንማውዝ ከ ኖርዊች እና ቡርቶን አልቢዮን ከ ኖቲንግሀም ፎረስት በአራተኛው ዙር ተገናኝተዋል፡፡

በወጣው መርሀ ግብር መሰረት ጨዋታዎቹ ጥቅምት 20/2011 ዓ/ም ይካሄዳሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button