AfricaEthiopiaPolitics

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለረዥም ዓመታት በሚሲዮኖች ሲሰሩ የነበሩ ከ90 በላይ ሰራተኞች ወደ አገር ቤት ጠራ

አርትስ 22/01/2011
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለረዥም ዓመታት በሚስዮኖች በአገልግሎት ዘርፍ ሲሰሩ የነበሩ ከ90 በላይ ሰራተኞችን ወደ አገር ቤት መጥራቱን የሚነስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ የሚጠበቁት እነዚህ ሰራተኞች ከ4 አስከ 25 ዓመታት በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ጽህፈት ቤቶች የቆዩ ናቸው።

ከዚህም በተጨማሪ 130 ዲፕሎማቶች አስፋላጊው ስልጠና ከተሰጣቸው በኃላ ሀገራቸውን በተለያዩ ኃላፊነቶች እንዲያገለግሉ ወደ ኤምባሲዎች መመደባቸውም ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጥንቶ ያቀረበው መዋቅር በፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር ከታየ በኃላ በጠቅላይ ሚንስትሩ በመጽደቁ በቅርቡ የዲፕሎማቶች ዳግም ምደባ የሚደረግ የሚደረግ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህም መሰረት በመስሪያ ቤቱ የሰው ሃይል ምደባ መስፈርት መሰረት በሁሉም ሚሲዮኖች የሚገኙ ዲፕሎማቶች ዳግም ምድባ የሚያካሂድ ሲሆን፥ ይህም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሙያ ክህሎት ያጠናክራል ተብሎ ታምኖበታል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button