EconomyEthiopiaPolitics

ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞትን ተከትሎ የግድቡን ግንባታ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን ላለፉት ሁለት ወራት በጊዚያዊነት ሲመሩት ቆይተዋል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ በዛሬው ዕለት ለግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች ኃላፊነት ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ከዛሬ ጀምሮ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ፣ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን እና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ገልጿል ኢቲቪ እንደዘገበው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button