Ethiopia

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፉ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፉ::በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቨገንሲ ተርክሂን ኢትዮጵያውያን የዛሬ 80 ዓመት ለተቀዳጁት ድል የሚታሰብበት የአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በዚህ ክስተት ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን ከፋሽስት ወረራ ነፃ ያወጡበት 80ኛ ዓመት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ብለዋል። በአውሮፓውያኑ 1935 የፋሺዝም ጭቆናን በመጋፈጥ በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን ያስታወሱት አምባሳደሩ ክስተቱ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ትንቢት የተናገረ ድል ስለመሆኑም
ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ የመንፈስ ጥንካሬ እና የነፃነት ፍላጎት እንዲሁም የቅኝ ግዛት እምቢተኝነት ለድል እንዳበቃቸው አምባሳደሩ አስታውሰዋል። ይህም ኢትዮጵያ ከፋሽስት ቀንበር ራሷን ነፃ በማውጣት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች ብለዋል። ይህ ታሪካዊ ትምህርትም የህዝቦች አንድነት፣ የመንፈስ ጥንካሬ እና ለነፃነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ግልፅ ያደርገዋል ያሉት አምባሳደሩ የትውልዱን ታሪካዊ ትውስታዎች ለማስጠበቅ ያለፉት ሀዘኖች ዳግም እንዳይከሰቱ መጠበቅ ተገቢ ነው ብለዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button