AfricaPolitics

የመንግስታቱ ድርጅት የኤርትራን ማዕቀብ በነገው ዕለት ሊያነሳ ነው

አርትስ 04/03/2011

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው  ምክር ቤት  በኤርትራ ላይ ላለፉት 10 ዓመታት  ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ለማንሳት ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተገለፀ፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችውን የሰላም ስምምነት እንዲሁም ከጅቡቲ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ያደረገችውን ጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት  ነው ማዕቀቡን ለማንሳት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ተደራድረው የጨረሱት፡፡

ሮይተርስ የድርጅቱን ዲፕሎማቶች ጠቅሶ እንደዘገበው ማዕቀቡን ለማንሳት በእንድሊዝ የቀረበውን ረቂቅ 15 የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላትያለልዩነት እንደሚቀበሉት ይጠበቃል፡፡

ኤርትራ የሶማሊያውን አልሸባብ  ለሚባለው ቡድን እገዛ ታደርጋለች በሚል እንደአውሮፓዊያኑ አቆጣተር በ2009 አ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀቡን እንደጣለባት ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button