SportSports

ማንችስተር ሲቲ በካራባዎ ዋንጫ በርተን አልቢዮን የግብ ናዳ በማዝነብ አሸነፈ

ማንችስተር ሲቲ በካራባዎ ዋንጫ በርተን አልቢዮን የግብ ናዳ በማዝነብ አሸነፈ

የ2018/19 የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ካፕ (ካራባዎ ዋንጫ) የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ትናንት ምሽት በኢቲሃድ ስታዲየም በፕሪምየር ሊጉ ቡድን ማንችስተር ሲቲና በሊግ አንድ ተሳታፊው በርተን አልቢዮን መካከል ተካሂዷል፡፡

በተካሄደው ጨዋታ የፔፕ ጓርዲዮላው ቡድን በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ አራት እንዲሁም በሁለተኛው አምስት ተጨማሪ ግቦችን በማከል 9 ለ 0 በሆነ ውጤት በአሰልጣኝ ኒጀል ክላፍ የሚመራውን በርተን አልቢዮንን ረምርሞታል፡፡

በምሽቱ ከተቆጠሩ ግቦች ብራዚላዊው ጋብርየል ጀሱስ አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር፣ ኬቭን ዴ ብሯይኔ፣ ኦሌክሳንድር ዚንቼንኮ፣ ፊል ፎደን፣ ካይል ዋከር እና ሪያድ ማህሬዝ ቀሪዎቹን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

ሲቲ በዚህ የግብ ልዩነት ማሸነፉን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ሊቨርፑል በወርሃ መስከረም 1986 ፉልሃም ላይ ካስመዘገበው የ10 ለ 0 የሊግ ካፕ ድል ቀጥሎ ከፍተኛ የግብ መጠን የተቆጠረበት ጨዋታ ሁኗል፡፡

ባለፈው ዕሁድ ሲቲ በኢምሬትስ ኤፍ ኤ ካፕ የሶስተኛ ዙር ጨዋታ ሮዘርሃም ዩናይትድ ላይ ሰባት ጎሎችን ያዘነበ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በአጠቃላይ በአራት ቀን ውስጥ 16 ጎሎችን በተቃራኒ ቡድን መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል፡፡

የግማሽ ፍፃሜው የመልስ ጨዋታ ከ13 ቀናት በኋላ በፔሬሊ ስታዲየም የሚከናወን ሲሆን በፍፃሜው ከቼልሲ እና ቶተንሃም አሸናፊ ጋር ይገናኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያ ቶተንሃም በዌምብሌ ቼልሲን በሃሪ ኬን አወዛጋቢ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ 1 ለ 0 መርታቱ ይታወሳል፡፡ የመልሱ ጨዋታ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ይከናወናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button