EconomyEthiopiaSocial

“በሬ ለምኔ” የተሰኘው ዘመናዊ ማረሻ ወደ ስራ ሊገባ ነው

አርትስ 28/01/2011

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራው በሬ ለምኔ የእርሻ ስራን በሬን ተክቶ ይሰራል፡፡

በሬ ለምኔ  በእጅ የሚገፋ ዘመናዊ ማረሻ  ሲሆን በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

ማረሻው የአርሶ አደሮችን ድካም በመቀነስ እርሻቸውን ከማቀላጠፉ በተጨማሪ አርሶ አደሮች ለእርሻ የሚጠቀሙባቸውን በሬዎች  በማደለብ ወደ ስጋ በመቀየር ገቢያቸው እንዲጨምር ያግዛል ።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ  ሚኒስትርሩ  ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ  የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱና ኑሯቸውን የሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ፈጠራን ማላመድ ላይ መስርያቤታቸዉ ትኩረት አድርጓል ብለዋል ።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button