EthiopiaRegionsSocial

በአሰላ ከተማ መናኸሪያ ዉስጥ ከ70 በላይ ሰለታማ መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተሰማ

አርትስ20/01/2011
የአሰላ ከተማ የወረዳ አንድ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኢንስፔክተር አብደላ ባቱና እንደተናገሩት ሸምሰዲን ከዶ የተባለ ተጠርጣሪ ከ70 በላይ ሰለታማ የሆኑ መሳሪያዎች ወይም ሳንጃዎችን በሻንጣ ይዞ ሲንቀሳቀስ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት በከተማዋ መናኸሪያ ዉስጥ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
የአሰላ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀዉ በአሁኑ ጊዜም ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተካሄደበት ነዉ፡፡
ኢንስፔክተሩ ያለ ህብረተሰብ ተሳትፎ የተረጋገጠ ሰላምን ማምጣት ስለማይቻል የከተማዋ ነዋሪም ለጸጥታ ስጋት ይሆናል ብሎ የሚጠረጥረዉ ነገር ካለ ጥቆማዉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button