Breaking News

ላለፉት 5 ዓመታት ታግዶ የነበረዉ ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ ሀገራት የሚደረገዉ ጉዞ ከነገ ጀምሮ በይፋ ይከፋታል፡፡

ላለፉት 5 ዓመታት ታግዶ የነበረዉ ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ ሀገራት የሚደረገዉ ጉዞ ከነገ ጀምሮ በይፋ ይከፋታል፡፡

አርትስ 30/01/2011
የስራ ስምሪቱ የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው ሀገሮች ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታርና ጆርዳን ተግባራዊ ይሆናል፡፡
የውጭ አገር የስራ ስምሪት መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም በይፋ እንደሚከፈት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መግለጫ እንዳመለከተው፣ የውጭ አገር የስራ ስምሪትን ለመጀመር የሚያስፈልጉት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቃቸው የውጭ አገር የስራ ስምሪት ስራዉን ይጀመራል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ስምሪት አዋጅ ቁጥር 104/90 እና አዋጅ ቁጥር 632/2001 አውጥቶ ሥራ ላይ አውሎ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ይሁንና አዋጁ በስራ ላይ በነበረበት ወቅት ወደ ውጭ ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች ተገቢው መብትና ክብራቸውን ከማስጠበቅ አኳያ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት የነበረበት በመሆኑ የውጭ አገር የስራ ስምሪት ከጥቅምት 14 ቀን 2006 ጀምሮ እንዲዘጋ ተድርጎ ቆይቷል፡፡
ይህንን ተከትሎ ወደ ውጭ አገር በመሄድ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሠርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተደረገው ዝግጅት፣ መንግስት የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡በአሁኑ ወቅትም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቃቸው ከተቀባይ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው ሀገሮች ስራዉን ይጀምራል፡፡
የመክፈቻ ስነስርዓቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሚገኙበት ይከወናል ተብሏል፡፡

leave a reply