EthiopiaPoliticsRegionsSocial

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለጋሞ አባቶች የነጭ ርግብ ምስል ስጦታ አበረከቱ

አርትስ 05/02/2011
የጋሞ አባቶች የግጭት አፈታት በርካታ አመታትን በፖለቲካው ዓለም አሳልፈው ስለበጎነትና ስለፍቅር መስበክ ለሚቸገሩ ፖለቲከኞች ትምህርት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በአርባ ምንጭ ከተማ ከጋሞ አባቶችጋር ባደረጉት ውይይት ላከናወኑት ተግባር እውቅና ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የጋሞ አባቶች ባለፈው በከተማው የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም ያደረጉት አስተዋጽኦ የሚያስመሰግናቸው ነው ብለዋል።
የጋሞ የሃገር ሽማግሌዎቹ እሴቶች በአግባቡ ተቀምረው በየዩኒቨርሲቲዎቹ እንዲተላለፉ እንደሚደረግ ተናግረው ዝቅ ብሎ ማስተማርንና መገሰጽን እንዲሁም ስለ ሰላም መስራትን ከሽማግሌዎቹ መማር እንደሚገባ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ እርጥብ ሳር የያዘች የነጭ እርግብ ምስል ያለበት ስጦታ ለሃገር ሽማግሌዎቹ ያበረከቱ ሲሆን አባቶቹም ለተሰጣቸው እውቅና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button