Breaking News

አድዋ ላይ ጣሊያንን ድል ያደረግነው በዘር ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመደራጀት ነው አሉ

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡

አቶ ኦባንግ ባህር ዳር ተገኝተው ከባሕር ዳር ወጣቶች ጋር ውይይት በደረጉበት ወቅት ˝ የዘር ፖለቲካ
የመጨረሻ ውጤቱ የጥላቻ እና ግጭት በሽታ መዝራት ነው ብለዋል፡፡
በዘር ፖለቲካ መደራጀት አጉል ፋሽን ሆኗል ያሉት አቶ ኦባንግ ኢትዮጵያዊነት ከጎሳ የበለጠ ትልቅ ሀይል
አለው፤የዘር ፖለቲካ የመጨረሻ ውጤቱ የጥላቻ እና ግጭት በሽታ መዝራት ነው፡፡ይህም ደግሞ ላለፉት
27 ዓመታት ቀምሰን አይተነዋል˝ በማለት ተናግረዋል፡፡
አቶ ኦባንግ አባቶቻችን አድዋ ላይ ጣሊያንን ድል ያደረጉት በዘር ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ
በመደራጀት ነው፤ሁላችንም ነጻ ካልወጣን አንዳችንም ነጻ ልንሆን አንችልም፤ለዚህ ደግሞ የመጨረሻ
ው ቁልፍ መንገድ ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ ሰብአዊ መብቱ እንዲከበር ማድረግ ስንችል ነው በማለት
ገልፀዋል፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶች በዘር እንደንከፋፈል ያደረግን ህገመንግስቱ
ነው፡፡አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ህገመንግስታዊ ማሻሻያዎችን ሊያደርግ ይገባል፤በብሄር
እንደንደራጅ የሚፈቅድ ህገመንግስት እስካለ ድረስ ሰዎች በቦታ መከፋፈላቸው የሚገርም አይደለም
ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ተወያዮቹ የዘር ፖለቲካ ሳንወድ በግድ የግለሰቦችን ስም እንድናጠና አስገድዶናል፤ይህ
ደግሞ ጥላቻ እንዲኖር መንገድ ከፍቷል ማለታቸዉን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

leave a reply