Breaking News

ቻይና ከአፍሪካ ዋነኛ አበዳሪ ተቋማት ተርታ የለችበትም ተባለ

ቻይና ከአፍሪካ ዋነኛ አበዳሪ ተቋማት ተርታ የለችበትም ተባለ

አፍሪካ ከዉጭ ሃገራት የምትበደረዉ የብድር መጠን ከፈረንጆቹ 2015 እስከ 2017 ድረስ በእጥፍ መጨመሩን ኢስት አፍሪካን የዘገበ ሲሆን ከ2001 ጀምሮም የአሃጉሪቱ የብድር መጠን  ጣሪያ ነክቷልም ብሏል፡፡

የአለም ባንክ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአፍሪካ ሃገራት ከዉጭ ከተበደሩት ዉስጥ 32 በመቶዉ  ከጎንዮሽ አበዳሪዎች 32 በመቶዉ ከግል አበዳሪዎችና 20 በመቶ የሚደርሰዉ ከቻይና የተገኘ ብድር ሲሆን 13 በመቶዉ ደግሞ ከሌሎች ሃገራት የተወሰደ ብድር ነዉ፡፡

አፍሪካ ካለባት 130 ቢሊዮን ዶላር የብድር እዳም 72 ቢሊዮን ዶላር የሚደርሰዉ ከቻይና የተገኘ ሲሆን 40 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ከፓሪስ ክለብ የተገኘ ነዉ፡፡ ቀሪዉ 18 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ከተለያዩ አለም ሃገራት ተገኘ ነዉ ሲል ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡  

 

leave a reply