EconomyEthiopiaPoliticsSocial

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በብድር የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች በጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ዕዳ ለመክፈል እንቅፋት ሆኖብናል አሉ

የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ሳናጠናቅቅ ሌሎች ፕሮጀክቶችን መጀመር የኢኮኖሚ ችግር እያስከተለብን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች በብድር ተጀምረው በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ብድሮችን ለመክፈል አዳጋች እንደሆነ አስታውቀዋል።

ከዚህ በኋላ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች መሆኑንና ለነዚህ ልዩ ድጋፍ በማድረግ ካጠናቀቀ በኋላ አገልግሎት ሲሰጡ ብቻ ሌሎች ፕሮጀክቶችን መጀመር ይቻላል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመንግስት ዓመታዊ ዕቅድ ዙሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንዳስታወቁት መንግስት የጀመራቸው የልማት ስራዎች አልተቋረጡም።

አዳዲስ ፕሮጀክቶች የዘገዩት የተጀመሩት እስኪጠናቀቁ በሚል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘንድሮ አመት ለመንገድ ግንባታ 38.5 ቢሊዮን ብር ፣ ለኤሌክትሪክ ሃይል ደግሞ 130 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ተናግረዋል።

የግል ባለሃብቶችን የኢንቨስትመንት ሴክተሮች ላይ በማሳተፍ በርካታ እድሎችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button