AfricaEthiopiaPoliticsRegions

የኤርትራና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች ጎንደር ገቡ

የኤርትራና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች ጎንደር ገቡ

አርትስ 30/02/2011

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ግብዣ በአማራ ክልል ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡
የዛሬው ጉብኝት በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ እየፈጠረ የሚገኘው የለውጥ እንቅስቃሴና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማመቻቸት ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሚያካሂዱት እንቅስቃሴ አካል እንደሆነም ተነግሯል ::
ባለፈው ወር በኤርትራ አስመራ የተካሄደው የሶስቱ አገራት የጋራ ምክክር ተከታይ የሆነው ይህ ጉብኝትም ፣ውይይቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት ስታውቋል፡፡
መሪዎቹ በጎንደርና ባህር ዳር የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎችን እንደሚጎበኙ እና ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ፎቶ ኤፍ ቢ ሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button