Breaking News

ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

አርትስ10/02/2011

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስልጠናውን ሲከፍቱ

አመራሩ ለውጡን ለማስቀጠል የማያቋርጥ የመማርና የማድረግ ሂደት ውስጥ መግባት እንዳለበት ተናግረዋል።

አመራሩ ለሚመራው ህዝብ ምሳሌ መሆን እንዳለበት ሲገልፁ ሰዓት በማክበር፣በትጋት በመስራት፣ ውጤታማ በመሆን እንዲሁም በሌሎች ህዝቡን በሚጠቅሙ መልካም ተግባራት ምሳሌ ሆኖ በማሳየት መሆን እንዳለበት መናገራቸውን የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልፀዋል።

እያንዳንዱ ሚንስትር የመጀመሪያ 100 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት ፈጣና የህዝቡን ፍላጎት የሚመጥን ለውጥ ለማምጣት እንዲረባረብም አሳስበዋል::

ስልጠናው ቁልፍ በሆኑ ርዕሶች፤ በተመረጡ የዘርፉ ምሁራን በመካሄድ ላይ ይገኛል:: ለሁለት ቀናትም ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል::

leave a reply