Uncategorized

ትራምፕ ሜክሲኮ ከጓቲማላ እየገቡ ያሉ ስደተኞችን እንድታስቆም አስጠነቀቁ

አርትስ 12/02/2011

ሜክሲኮ ከጓቲማላ እየፈለሱ ያሉ  ሰዎችን ካላስቆመች ከሜክሲኮ ጋር ባላት ድንበር ላይ ጦር እንደሚያቆሙ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።

ባለፈው ሣምንት ከሆንዱራስ የተነሡ ሦስት ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች  ጓቲማላንና ሜክሲኮን አቋርጠው ወደ አሜሪካ መግባታቸውን ገልፀው ከእነዚህ ስደተኞች መካከል ወንጀለኞች  መኖራቸውን እና  ሜክሲኮ ይህን የማታስቆም ከሆነ አሜሪካ በሃገራቱ ድንበር ላይ ጠባቂዎችን እንደምታቆም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ  ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ድንበሯ ላይ የሚጣሉ ጥቃቶች ከካናዳና ከሜክሲኮ ጋር የገባችባቸውን የንግድ ውሎችንም ይጎዳሉ ነው ያሉት፡፡

እንደ  ሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ  የትራምፕን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ከጓቲማላ በሜክሲኮ ድንበር የሚገቡ ስደተኞች በመጠለያ ፍለጋ እየተንከራተቱ ነው ተብሏል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button