EthiopiaPoliticsSocial

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እና ውይይት ተጠናቀቀ

አርትስ12/02/2011

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ20ውም የሚኒስቴር መ/ቤት የሚጠበቁ ያሏቸውን ዋና ዋና የውጤት አመልካቾችን ባጭሩ ገልጸው እነዚህ ተዘርዝረው በየሚኒስቴር መ/ቤቱ የ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ እንዲካተቱ አመራር ስጥተዋል::

የተዋሃዱ የሚንስቴር መ/ቤቶች ወይም ተጠሪዎች ወይም ሌላ የተልዕኮ ወይም የአደረጃጀት ለውጥ የተደረገባቸው ተቋማት ፈጥነው በማስተካከልና ለሰራተኞቻቸው በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል:: በቢሮና ንብረት ርክክብ ብዙ ጊዜ መባከን እንደሌለበትም አስገንዝበዋል::

እንደምሳሌ:-

1) የሰላም ሚኒስቴር :-

* ሰላምና ደህንነትን የማረጋገጥ
* ብሔራዊ መግባባትን የማስፈን
* ግጭቶችን የመፍታትና የማስወገድ
* የዲሞክራቲክ ተቋትማን አሰራር የማዘመን

2) የመከላከያ ሚኒስቴር:-

* ጠላት የመከላከል ብቃትን የማሳደግ
* ብቃት ያለው የመከላከያ የሰው ኃይል የማዘጋጀት * ባህር ኃይልን የማደራጀት

3) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር:-

* ከጎረቤት እንዲሁም ከሌሎች ስትራቴጂክ ከሆኑ አገሮች ጋር ወዳጅነትን የማጠናከር
* የዳያስፖራ ተሳትፎን በሙያም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የማጠናከር
* ውጭ የሚኖሩ ዜጎችን መብት የማስከበር
* የአገሪቱን ገጽታ የመገንባት
* የዲፕሎማቶች እና የሌሎች ሙያተኞችን ስምሪትን የማሻሻል

4) የገንዘብ ሚኒስቴር

* የኃብት ምንጭን የማሳደግ
* ብድር የመክፈል አቅምን የማሻሻል: የኮሜርሺያል ብድር ወደ ኮንሴሽናል ብድር እንዲቀየር የመስራት
* ወደግል መዞር የሚገባቸውን ተቋትማት ህጉን ተከትሎ እንዲዛወሩ የማድረግ
* የዋጋ ንረትን /ግሽበትን የመቆጣጠር

5) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

* የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ
* የህግና ፍትህ ሪፎርምን በብቃት የመምራት (የሚሻሻሉ ህጎችን ማሻሻልን ጨምሮ)
* የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት የማክበር: በህጉ መሰረትም እንዲታረሙ የማድረግ

6) ግብርና ሚኒስቴር

* ዘርፉ በርካታ ተግባራትን በመያዝ የተደራጀ በመሆኑ በአግባቡ በሚ/ር መ/ቤቱ ውስጥም ሆነ ከሌሎች ጋር አቀናጅቶ የመምራት
* የግብርና ዘርፉን ምርታማነት የማሻሻል:
* የማዳበሪያ: የምርጥ ዘርና ሌሎችም ግብዓቶችን በወቅቱና በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ:

የሚሉት በምሳሌ ደረጃ ተጠቃሽ ናቸው::

በመጨረሻም በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች የስራ ጊዜን በማይሻማ መልኩ ከየተልዕኮአቸው ጋር የተቃኘ ስልጠና ሊሰጥ እንደሚገባ ተገልጾ ስልጠናው ተጠናቋል።
የጠ/ሚኒስቴር ፅ/ቤት ኃላፊ ፍፁም አረጋ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close