EconomyEthiopiaPoliticsSocial

የአገሪቱ የወጪ ገቢ ንግድ በጥቂት ግለሰቦች መያዙ በጥናት ተረጋገጠ

በቤተሰብ የተያዙ 5 ወይም 6 የሚሆኑ የንግድ ተቋማት አጠቃላይ የአገሪቱን የወጪ ገቢ ንግድ እንደሚቆጣጠሩት የፌደራል እምባ ጠባቂ ተቋም የሰራው ጥናት አመለከተ᎓᎓

 

የፌደራል እምባ ጠባቂ ተቋም በአዲስ አበባ በሸማቾች ላይ የሚደርሰውን የዋጋ ንረት በተመለከተ ባስጠናው ጥናት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በቢሾፍቱ በተካሄደው መድረክ ለሸቀጥ ዋጋ መናር ምክንያት በሆኑ ደላሎች፣ ዋጋን በምክር የሚወስኑ አድመኛ ነጋዴዎችና ያልተገባ ጥቅም ለማግበስበስ ሲሉ በሚተባበሯቸውየመንግሥት ተቆጣጣሪ አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወስድ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጠይቋል።

በአገሪቱ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በንግድ ሂደቱ ላይ ህገወጥ ድርጊቶች ይታያሉ በዚህም ምክንያት ሸማቹን ኅብረተሰብ ሊቋቋመው ወደማይችለው የኑሮ ውድነት እየተገፋ ነውብለዋል።

የትርፍ ህዳግ አለመኖር አንድ ነጋዴ በ100 ብር የሚሸጠውን እቃ እስከ 1000 ሺሀ ብር የመሸጥ መብት እንደሚሰጥና ይህም ሸማቹን እየጎዳ እንደሚገኝ ተነስቷል᎓᎓

መንግሥት ያደረገው የውጭ ምንዛሪ ማስተካከያ 15 በመቶ ሆኖ እያለ አብዛኛዎቹ ጭማሪዎች ግን ከ30 እስከ 50 በመቶ መድረሳቸው በጥናቱ ግኝት ውስጥ ተካቷል።

ጥናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ጥናቱ የሥራ ኃላፊዎችን፣ ሠራተኞችን ነጋዴዎችንና ሸማቶችን ጨምሮ 1ሺ 98 ሰዎች በመጠየቅና በውይይት አሳትፏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button