EthiopiaRegionsSocial

የላልይበላን አብያተ ክርስትያናት ለመጠገን ሶስት ዓመት ይፈጃል ተባለ

አርትስ 14/02/2011

 የላልይበላን አብያተ ክርስትያናት ለመጠገን የሚያስችለው ገንዘብ ከተገኘ ጥገናው ሶስት አመት እንደሚፈጅ የአማራ ክልል የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ልዑል ዩሐንስ እንደሚሉት የብዙዎች ስጋት እና ትልቁ ፈተና ቅርሱ ላይ ያለውን ጣሪያ እንዴት እናነሳዋለን የሚለው ጉዳይ ነው።

ነገር ግን  ጣሪያው እንዴት ሊነሳ እንደሚችል ጥናቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ቅርሶቹ አደጋ ላይ እያሉ ሳይጠገኑ እስከ ሶስት ዓመት እንዴት ሊቆዩ ይችላሉ የሚለውን ጥያቄ ብዙዎች ይጠይቃሉ ያሉት አቶ ልዑል ነገር ግን የቅርስ ጥገና ገንዘብ ስለተገኘ ብቻወዲያው የሚገባበት ስራ ባለመሆኑ ጥንቃቄ ይፈልጋል ነው ያሉት ።የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button