Breaking News

የአውሮፓ እና የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ተቀራርበው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ተባለ

የአውሮፓ እና የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ተቀራርበው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ተባለ

አርትስ 15/02/2011

ይህ የተባለው የዘንድሮውን የአውሮፓ ፊልም ፌስቲቫል   አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡

ከአውሮፓ  ሀገራት   የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኙ እና የተመረጡ 20 ፊልሞች ናቸው ለታዳሚያን የሚቀርቡት፡፡

ፊልሞቹ የአውሮፓን ባህል ፤ጥበብ እና ታሪክ ይዳስሳሉ ተብለው የተመረጡ ናቸው ያሉት  የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር  ጆሃን ቦርግስታም ፤ በፌስቲቫሉ የኢትዮጵያ አጫጭር ፊልሞችም ለዕይታ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡

ይህም የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ፊልም ሰሪዎች ልምድ እንዲለዋወጡ ዕድል ይፈጥራል ነው የተባለው፡፡

ፌስቲቫሉ  ከፊታችን ጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 25 እንዲሁም ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 02 ድረስ እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡

leave a reply