Breaking News

ለሁሉም አፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት ሊጀመር ነው

ለሁሉም አፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት ሊጀመር ነው

ለሁሉም አፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት ሊጀመር ነው

አርትስ 16/02/2011

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ቦጋለ  እንደገለጹት በኢትዮጲያ ለሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት በሚቀጥለው ሳምንትይጀመራል ።

የመዳረሻ ቪዛው ለአፍሪካ አገራት ዜጎች መሰጠቱ ለአገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ለ 37 የተለያዩ የአለም ሃገራት እና ለደቡብ አፍሪካ ብቻ ይሰጥ የነበረው የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ በሙሉ የአገልግሎት ሥርዓቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ  ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

 የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎቱ ለአፍሪካ ሀገራት ዜጎች መሰጠቱ ለአገሪቱ ቱሪዝም ዕድገት መልካም   አጋጣሚ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡

leave a reply