Breaking News

በአማራ ከልል የተካሄዱ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸው ተገለፀ

በአማራ ከልል የተካሄዱ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸው ተገለፀ

በአማራ ከልል የተካሄዱ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸው ተገለፀ

አርትስ 19/02/2011

በትናንትናውዕለት  በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በወልዲያ፣ በደብረ ብርሀን፣ በደብረ ታቦር፣ በሰቆጣ፣ በሀይቅ፣ በደሴ እና ሌሎችም ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደው ሁሉምበሰለጠነ እና በሰላማዊ መንገድ መልዕክት በማስተላለፍ ተጠናቀዋል ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአርትስ ተናግረዋል፡፡
በሰልፎቹ ላይ አራት ዋና ዋና መልዕክቶች ለመንግስት ተላልፈዋል ብለዋል :: መልዕክቶቹም  የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ምላሽ ይሰጠው፤ የራያ ህዝብየማንነት ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ምላሽ ይሰጠው፤ የላልይበላ ቅርሶች መፍትሄ ይሰጣቸው የሚሉ እና  የጣና የእምቦጭ አረም መፍትሄ ይሰጠው የሚሉ ናቸው::

leave a reply