EducationEthiopia

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ክልል ውጭ መማር የለባቸውም በሚል መሪ ሃሳብ በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ክልል ውጭ መማር የለባቸውም በሚል መሪ ሃሳብ በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

አርትስ 19/02/2011

 

ሃገሪቱ ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ክልል ውጭ መማር የለባቸውም በሚል መሪ ሃሳብ በትላንትናው እለት የመቀሌከተማ ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

የሰልፈኞቹ ጥያቄ  በሃገሪቱ በየክልሎች የሚስተዋሉት ችግሮች ተማሪዎቹ ደህንነታቸው ተረጋግጦ ያለስጋት እንዳይማሩ እንቅፋት ስለሚሆን እና ለህይወታቸውም አስጊ በመሆኑ የሚስተዋሉት ችግሮች በመንግስት መፍትሄ እስከሚያገኙ  በሌሎች ክልሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመደቡ ተማሪዎች   በሚኖሩበት ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ገብተው እንዲማሩ የሚል ነው፡፡

በሌላ በኩል   የክልሉ ርዕሰ – መስተዳድር ዶ/ር ድብረፅዮን ገብረሚካኤል በሰጡት መግለጫ ልጆቻቸውን ወደ ትግራይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚልኩ በየትኛውምየሀገሪቱ ክፍል ያሉ ወላጆች ሥጋት እንዳያድርባቸው እና የትምህርቱን ዘመን ሰላማዊ ለማድረግ እየተካሄደ ያለው ዝግጅት እየተጠናቀቀ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደቤተሰቦቻቸው እንደላኩ ይቁጠሩት ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button