EthiopiaPoliticsSocial

አቶ ደበሌ ቃበታ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆኑ

አርትስ 19/02/2011

 

የገቢዎች ሚኒስቴር የ2011 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቢሾፍ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ተቋሙ በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊለውጥ የሚያግዝ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት መዘርጋት አለበት፡፡

ይህንንም ለማሳካት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከሚመለካተቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ከምንግዜውም በላይ ማጠናከርአለበት ብለዋል፡፡

በተለያዩ የመንግስት አሠራሮች ላይ እየተደረገ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ የሚስተካከል የሪፎርም ስራ በቀጣይ ይሰራልም ብለዋል፡፡በተጨማሪምመላው ሰራተኛና የስራ ኃላፊዎች በተነሳሳ መንፈስ በጋራ ለለውጥ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ከእንግዲህ ሰው የሚለካው በስራው ውጤት እና ውጤት ብቻ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ በተለይም የሰው ሃይል የመፈፀም አቅምን ከማሳደግጀምሮ የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን እንደሚሠሩም ተናግረዋል፡፡

ለገቢ እቅዱ አፈፃፀም የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዛሬው ውሎው አቶ ደበሌ ቃበታን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጓቸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button