Africa

ናይሮቢ በኬንያ አየር መንገድ ወደአሜሪካ መብረር ፌሽታ ላይ ናት

ናይሮቢ በኬንያ አየር መንገድ ወደአሜሪካ መብረር ፌሽታ ላይ ናት

አርትስ 20/02/2018

የኬንያ አየርመንገድ ወደአሜሪካዋ ከተማ ኒውዮርክ ለመብረር ሲዘጋጅ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጆሞ ኬንያታ አየር ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውለታል።

 

የቀጥታ በረራው በኬንያ አቪዬሽን ታሪክ የመጀመሪያው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው አውሮፕላኑ በልዩ ስነስርዓት ሽኝት የተደረገለት። ከበረራው አንድ ቀን ቀደም ብሎም አየርመንገዱና አካባቢው በጥብቅየደህንንነት ጥበቃ ስር ውለዋል ።

 

በውጭጉዳይ ሚኒስትሯ ሞኒካ ጁማ የተመራ የልዑካን ቡድንን አሳፍሮ  ወደአሜሪካ ጉዞውን ያቀናው ይኸው ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን  በህብረ ዘማሪያንና በማርሽ ባንድ ሙዚቃዎች ታጅቦነበር ያኮበኮበው።

 

ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን በመምራት በሽኝቱ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ቀጥታ በረራው ኬንያን ከተቀረው አለም ጋ የሚያገናኝ ድልድይ ነው ብለውታል።

 

ከመነሻው ሁለት ሰዓት ያህል ዘግይቶ ጉዞውን የጀመረው አውሮፕላኑ ትናንት ቀትር ላይ ኒውዮርክ ጆንኤፍ ኬኔዲ አውሮፕላን መድረሱም ተረጋግጧል።

 

በተያያዘ መረጃ የአህጉሪቱ ግዙፍ አየርመንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደኒውዮርክ ቀጥታ በረራ የጀመረው ከሁለት አመታት በፊት ነበር። አየርመንገዱ በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ በቀጥታየሚበርርባቸውን የአሜሪካ ከተሞች ቁጥር 12 ማድረስ ችሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button