EducationEthiopiaRegionsSocial

በአዲስ አበባ ስምንት ት/ቤቶች በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 2800 ተማሪዎችን እያስተማሩ ነው

አርትስ 21/02/2011

በቅርቡ በመዲናችን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ መንግስት በወሰነው መሰረት ትምህርት ቤቶቹ በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበውበማስተማር ላይ መሆናቸውን ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ መደረጉ ተገቢ መሆኑን የገለጹት ተማሪዎችና መምህራን እንደ መጽሐፍና የመማሪያ ክፍሎች ያሉ እጥረቶች ትኩረት ሊያገኙይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ በዚህ የትምህርት ዘመን በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ በ8 ትምህርት ቤቶች በአፋን ኦሮሞየመማር መስተማር ሂደት መቀጠሉን የትምህርት ቢሮው ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ታከለ ከበደ ገልጸዋል፡፡

በንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማም 1 ትምህርት ቤት በቅርቡ በአፋን ኦሮሞ የማስተማር ስራ እንደሚጀምር ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የመማሪያ ክፍሎች እጥረትን ለመፍታት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ከመጽሐፍት እጥረት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር በተመለከተ እስከ መጀመሪያውሴሚስተር መጨረሻ ድረስ መጽሐፍት ታትመው እንደሚከፋፈሉ ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button