Uncategorized

ኦስትሪያ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ስምምነትን አልፈርምም አለች

አርትስ 21/02/2011

ኦስትሪያ ከሉዓላዊነት ጋር በተያያዘ ምክንያት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ስምምነት እንደማትፈርም እና ከስምምነቱ እንደወጣች አስታውቃለች።

ኦስትሪያ የመንግስታቱን ድርጅት የስደተኞች ስምምነት ከአሜሪካና ሃንጋሪ ቀጥሎ አልፈርምም ያለች 3ኛዋ ሃገር ናት፡፡

የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ ይህ ከመጭው ታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የመንግስታቱ ድርጅት ከስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መብት ጋር የተያያዘው ስምምነት ከሃገር ሉአላዊነት ጋር በተያያዘ ምክንያት እንደማይፈርሙ እና ድርጅቱ በሞሮኮ ማራከቺ በሚያደርገው ጉባኤ ላይ ተወካይዋን እንደማትልክ ገልፀዋል፡፡

ሮይተርስ እንዳስነበበው ይህንኑ የመንግስታቱን ድርጅት ስምምነት አስመልክቶ ሰባስቲያን ከርዝ በዛሬው እለት ከካቢኔያቸው ጋር ውሳኔ እንደሚያሳልፉም ይጠበቃል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ስምምነት ባለፈው አመት አሻፈረኝ ብላ ከወጣቸው ከአሜሪካ በስተቀር በ193 ቱም አባል ሃገራት መፅደቁ ይታወሳል፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button