EthiopiaPolitics

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆኑ

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆኑ

አርትስ 22/02/2011
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 5ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 4ተኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ በጉባዔውም ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ወስኗል፡፡
ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ማን ናቸዉ?
ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተወልደው ያደጉት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም በአሶሳ ከተማ ነው፡፡ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ አግኝተዋል፡፡ ከአሶሳ ወጥተው አዲስ አበባ ከተማን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጡት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ለመማር ተመድበው በመጡበት ጊዜ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ መጀመሪያ ወደ ሥራው ዓለም የቀላቀሉት ንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡ ንግድ ሚኒስቴርን ከለቀቁ በኋላ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ብዙም ያልገፉበትን የዳኝነት ሥራ ለቀው በሕገ መንግሥት ኮሚሽን ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በተለይ በሕገ መንግሥት ኮሚሽን መሥራታቸው ይበልጥ የሚታወቁበትን የሴት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበርን ለመመሥረት ዕድል ያገኙበት ነበር፡፡ እንደ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ያሉ ድርጅቶችም ሠርተዋል፡፡ በ11 ሴቶች አደራጅነት የተቋቋመው የእናት ባንክ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button