EthiopiaPoliticsSocial

ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በኋላ መሰረታዊ ለውጥ እንደምታሳይ ተስፋ አለኝ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በኋላ መሰረታዊ ለውጥ እንደምታሳይ ተስፋ አለኝ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

አርትስ 22/02/2011

ከ10 ዓመታት በኋላ ችግሮቿን ሁሉ ታሪክ ያደረገች የማትፈርስ የማትቀለበስ ኢትዮጵያን ለማየት ተስፋ አለኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በአውሮፓ ጉብኝታቸው ማጠቃለያ ላይ ጀርመን ፍራንክፈርት ውስጥ ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለታዳሚው ባሰሙት ንግግር ነው በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ተስፋና እምነት የገለጹት።

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ህይወታቸውን ገብረው ወደአውሮፓ ለመሻገር የሚያደርጉት አደገኛ ጉዞ ቀርቶ ስደታቸውም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያከትም ያላቸውን ተስፋና እምነትም ገልጸዋል። ፍልሰቱ ወደአውሮፓ መሆኑ ቀርቶ ወደኢትዮጵያ ይሆናል ነው ያሉት ።

በስደት ሃገራቸውን ጥለው የወጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ወደሃገራቸው የሚመለሱበት ጊዜ እንደማይርቅም ተስፋ አደርጋለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ልጆቻችን ወደአውሮፓ ለጉብኝት እንጂ ለስደት የማይጓዙበት ጊዜ ይመጣል ነው ያሉት።

ልጆቻችን ዛሬ በሰራነው መልካም ተግባርም ነገ ስማችንን በክብር እንደሚጠሩ አምናለሁ ብለዋል።

ከአስር ዓመት በኋላ የአፍሪካ ኩራት የሆነች፣ ለሁላችንም የምትበቃ ፣ ለሌሎችም የምትተርፍ የዓለም ፈርጥ የሆነች ኢትዮጵያን አያለሁ በማለትም ተስፋቸውን ለታዳሚው አጋርተዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button