SportSports

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል

አርትስ ስፖርት 23/02/2011

የ2018 የቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያ ዛሬ የሚከናወን ሲሆን ጨዋታው በግብፅ አሌክሳንድርያ ቦርጅ አል አረብ ስታዲየምበግብፁ አል አህሊ እና በቱኒዚያው ኤስፔራንስ ስፖርቲቭ ደ ቱኒስ መካከል ምሽት 4፡00 ስዓት ላይ ይደረጋል፡፡ በዛሬው የመጀመሪያ የፍፃሜ ጨዋታበቦርጅ አል አረብ ስታዲየም ከ60,000 በላይ ተመልካች ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ አል አህሊ ለዘጠንኛ እንዲሁምኤስፔራንስ ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡ ጨዋታውን በመሀል ዳኛነት አልጀሪያዊው አልቢትር አቢድ ቻሬፍ ሜህዲ ይመሩታል፡፡ የመልሱግጥሚያ ቱኒዚያ ላይ ቀጣይ ሳምንት አርብ ይደረጋል፤ ከዚያ አጠቃላይ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን የውድድሩን ዋንጫ ያነሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button