Breaking News

ትራምፕ ሳዑዲ አረቢያ የአሜሪካ ቦምቦችን እንዴት መጠቀም እንደምትችል አታውቅም በማለት ወቀሷት

ትራምፕ ሳዑዲ አረቢያ የአሜሪካ ቦምቦችን እንዴት መጠቀም እንደምትችል አታውቅም በማለት ወቀሷት

ትራምፕ ሳዑዲ አረቢያ የአሜሪካ ቦምቦችን እንዴት መጠቀም እንደምትችል አታውቅም በማለት ወቀሷት

አርትስ 26/02/2011

 ትራምፕ ይህንን ያሉት ባለፈው ነሃሴ ወር የሳዑዲ መራሹ ሃይል የጦር ጀት በአንድ የተማሪዎች አውቶቡስ ላይ ቦምብ ጥሎ 51  ሰዎችን  መግደሉን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት አስተያየት ነው።

40 ህጻናት በተገደሉበት በዚሁ የቦምብ ድብደባ ሳዑዲ መራሹ ጦር የተጠቀመው የአሜሪካን ቦምብ እንደነበር ተነግሯል።

ትራምፕ በዚሁ ጉዳይ ላይ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት አስተያየት ሳዑዲ የአሜሪካ ቦምቦችን እንዴት መጠቀም እንዳለባት እንኳን አታውቅም በማለት አንጓጠዋታል።

በቦምብ የተመታውን አውቶብስና የሞቱትን ህጻናት ለተመለከተ ሰው ሁኔታው ልክ እንደአስፈሪ ፊልም ደስ የማይል ነው ብልዋል ትራምፕ።

ትራምፕ አሜሪካ ለሳዑዲ መሳሪያ መሸጧ ስለሚያስከትለው ጥፋት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ባለፈው ሳምንት ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ በአሜሪካ የሚደገፈው ሳዑዲ መራሽ ጦር በየመን ላይ የሚያደርገውን ጦርነት እንዲያቆም አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች በማለት ዘግቦ ነበር።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ግን አሜሪካ ሳዑዲ መራሹን ጦር ትደግፋለች የሚለውን የጋዜጣውን ዘገባ አጣጥለውታል።

leave a reply