EducationEthiopiaPoliticsSocial

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያግዙ አራት ማሽኖችን አስመረቀ

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያግዙ አራት ማሽኖችን አስመረቀ

አርትስ 26/02/2011

 በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰራው ማሽን 19 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደወጣበት ተገልጿል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የዩኒቨርሲቲው ምሁራንና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝቷል፡፡

ማሽኖቹ አረሙን የሚሰበስቡ፣ የተሰበሰበውን የሚያጓጉዙ እንዲሁም ከሐይቁ ዳርቻ የሚያወጡ ናቸው የተባለ ሲሆን፥ የሙከራ ስራቸውንም ዛሬ ጀምረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ አረሙን ከሐይቁ ላይ ለማስወገድ የሰው ጉልበት ከመጠቀም በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ጉልበት የሚያግዙ ማሽኖችን በመጠቀም ስጋቱን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ ዩኒቨርስቲው ሐይቁን ከአረም ለመከላከል ተቋሙ ካሰራቸው ማሽኖች በተጨማሪ በምርምር የታገዘ ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንምአስታውቀዋል፡፡ ኢዜአ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button