Breaking News

ጀግኒት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ተካሄደ

ጀግኒት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አርትስ 26/02/2011

“ጀግኒት ታልማለች፤ ጀግኒት ታቅዳለች፤ ጀግኒት ታሳከለች”  በሚል አላማ  ሀገር አቀፍ የሴቶች የሰላም ንቅናቄ ዛሬ ተካሄዷል፡፡

˝ሴቶች ዘረኝነትን በመጠየፍ  ለሰላማችን ግንባር ቀደም ሚናችንን እንወጣ ˝ በሚል መሪ ቃል  የተዘጋጀው ንቅናቄ አላማው ህብረተሰቡ ለሴቶች ያለውን የተዛባ አመለካከት በመቀየር እና የኢትዮጵያ ሴቶች  ለሀገር ብልፅግና  የሚያበረክቱትን ሚና ለማጉላት  እንደሆነ  የሴቶች የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትሯ  ወይዘሮ የአለም ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

ይህ ንቅናቄ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ የተረጋገጠበት  በመሆኑ እና 50 በመቶ የካቢኔ አባለት  ሴቶች በመሆናቸው  ንቅናቄውን የተለየ ያደርገዋል ብለዋል ኃላፊዋ ፡፡

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የሴቶች ንቅናቄ ጥምረት የሴቶች የህፃናት እና  ወጣቶች  ሚኒስቴር
ያዘጋጀው ሲሆን ፤በቅርቡ የተሾሙት 10 ሚኒስትሮች የክልል ተወካዮች  አትሌቶች ፤ ሴት አመራሮች ተጽእኖ ፈጣሪዎች  የሃይማኖት አባቶች  እና  የመከላክያ ሰራዊት  አባላት  በተገኙበት  የጥምረቱ መመስረት ይፋ ሆኗል ፡፡

ጀግኒት የሰላም ንቅናቄ ጥምረት   ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ አደረጃጀት ለመመስረት መታቀዱን  ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

leave a reply