Uncategorized

ያደጉት ሀገራት ወንዶች በቆዳ ካንሰር እየተጠቁ ነው

አርትስ 26/02/2011

በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በኢኮኖሚ በበለፀጉ ሀገራት ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በቆዳ ካንሰር የመሞት እድላቸው ከፍ ብሏል፡፡

ጥናት ከተደረገባቸው 18 ሀገራት መካከል በስምንቱ የወንዶች በቆዳ ካንሰር የመሞት መጠን በ50 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው በተለይ በአየርላንድ እና በክሮሺያ በ 30 ዓመታት ውስጥ ችግሩ በእጥፍ አድጎ 70 በመቶ ደርሷል፡፡

በወንዶቹ እና በሴቶቹ መካከል ልዩነቱ ለምን እንደተፈጠረ ጥናቱ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ባይሰጥም ወንዶች ከሴቶች ያነሰ ቆዳቸውን የመንከባከብ ልምድ ስላላቸው ነው የሚለው መላ ምት አይሏል ነው የተባለው፡፡

በሮያል ፍሪ ለንደን ሆስፒታል ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ዶሮቲ ያንግ ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ቆዳቸውን ለፀሀይ ብርሀን ስለሚያጋልጡ  ነው ለችግሩ በቀላሉ የሚጋለጡት ብለዋል፡፡

ሳይንቲስቶች ነገሩ ቢያሳስባቸው የችግሩን መንስኤ ከመነሻው መርምሮ ለማወቅና መፍትሄ ለማፈላለግ ሌት ተቀን አየጣሩ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button