EthiopiaPolitics

አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

አርትስ 27/02/2011

አቶ ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ነው አቶ እንደሻው ጣሰው  የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት፡፡
አቶ እንደሻው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከሐገር ውጭ ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ከ1983 ጀምሮ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን  ከመከላከያ በኋላ   በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close