Breaking News

ዶ/ር ደብረፅዮን በአላማጣ “ብዙ ከመናገር ብዙ መስራት” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ውይይት ላይ ተገኙ

ዶ/ር ደብረፅዮን በአላማጣ “ብዙ ከመናገር ብዙ መስራት” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ውይይት ላይ ተገኙ

ዶ/ር ደብረፅዮን በአላማጣ “ብዙ ከመናገር ብዙ መስራት” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ውይይት ላይ ተገኙ

አርትስ 29/02/2011

  በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት “ብዙ ከመናገር ብዙ መስራት”  በሚል መሪ ቃል ለ3 ቀናት የሚቆየው ውይይት መካሄድ ጀምሯል፡፡

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ረዳዒ ኃለፎም እና ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች የተገኙበት ይህ ውይይት   በወቅታዊ ጉዳዮች ላይና በአካባቢው ባለው የልማት እንቅስቃሴ ላይ በይበልጥ መክሯል፡፡

በውይይቱ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡

በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ፣በመብራት ዝርጋታ፣ በህብረተሰብ  ተጠቃሚነት እና የፍትህ አሰጣጥ ስርዓት ላይ ያሉ ክፍተቶች ተደጋግመው የተነሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡

leave a reply