Uncategorized

ካሊፎርኒያ ውስጥ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ 13 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል

አርትስ 29/02/2011

 

ማንነቱ ያልታወቀው ይህ ግለሰብ በአንድ ቡና ቤት በሚዝናኑ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ አንድ የፖሊስ መኮንን እና 12 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፡፡

ቢቢሲ የዓይን እማኞችንና ፖሊስን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 10 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ጥቃት አድራሹ ግለሰብ በቡና ቤቱ ውስጥ ተገድሎ የተገኘ ሲሆን እስካሁን ማንነቱ አልታወቀም፤ድርጊቱን ለምን እንደፈፀመውም ፍንጭ አልተገኘም ብሏል፡፡

ፖሊስ ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ ምናልባት ራሱን አጥፍቶ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለው፡፡

ግለሰቡ ጥቃቱን ባደረሰበት ወቅት በቡና ቤቱ ውስጥ ከ200 ሰዎች በላይ በመዝናናት ላይ ነበሩ ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button