Breaking News

ግብፅ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ህግ ልታሻሽል ነዉ

ግብፅ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ህግ ልታሻሽል ነዉ

ግብፅ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ህግ ልታሻሽል ነዉ

አርትስ 30/02/2011

በፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናቱ እንደተጀመረ የተነገረለት አዲሱ የህግ ረቂቅ ሀሳብ በሰብዓዊ መበት ተሟጋቾች ትችት ደርሶበታል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የትችቱ ዋነኛ መነሻ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ የሚገድብ ነው የሚል ነው፡፡

አልሲሲ በፈረንጆቹ 2017 ሲቪል ሶሳይቲ ተቋማት በመብት ዙሪያ መስራት እንዳይችሉና አሰራራቸውን አጥብቆ የሚቆጣጠር ህግ በስራ ላይ እንዲውል በፊርማቸው አጽድቀው ነበር፡፡

በተጨማሪም ይህን አዋጅ ተላልፈው በተገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶች ላይ 55 ሺህ የአሜሪካን ዶላርና አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት የሚደነግግ ነው፡፡

ግብፅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  በበርካታ የመብት ተሟጋቾች ዘንድ  በየጊዜው አፋኝ ህጎችን  ታወጣለች የሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ ይደርስባታል፡፡

 

leave a reply